ETHIOPIAN NATIONAL DIALOGUE COMMISSION/የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን’s
Ethiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
በጋራ ሮጠናል፤ በጋራ እንመክራለን- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
ሀምሌ 5/2018 ዓ.ም
“ኢትዮጵያ እየመከረች ነው” በሚል መሪ ሃሳብ የተከናወነው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በስኬት ተጠናቋል።
በጎዳና ላይ ሩጫው ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ ሴቶች፣ የግልና የመንግሥት ሠራተኞች፣ የኤምባሲዎች ተወካዮች፣ ታዋቂ አትሌቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።
በመርሐግብሩ ላይ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ደምቀው ታይተዋል። የምክክር ድምጾች ከፍ ብለው ተደምጠዋል። ሁሉም በምክክር ስሜት በጋራ በመሮጥ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።
ኢትዮጵያዊያን በሕብረት አጊጠን በጋራ ሮጠናል፤ በጋራ እንመክራለ፤ ለዚህም ዜጎች በጎዳና ላይ ሩጫው ያሳዩትን የጋራ መንፈስ በምክክር ጉባኤው ወቅትም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል፡፡
የጎዳና ላይ ሩጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለተረባረቡት የኮሚሽኑ ሠራተኞች፣ የመንግሥት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች እና የጸጥታ ኃይሎች ኮሚሽኑ ምስጋና ያቀርባል።
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
